Benchmarks
View scores and output across OCR models spanning many document categories.
Want to run these evals on your own documents?
Talk to Salesየፅዳት ደህንነት መጠበቂያ ምክሮች ወረቀት
በፅዳት ኢንዱስትሪ ላይ ከሰራ ጋር የተያያዙ ጉዳቶችን ለመከላከል ተከታታይ የጤናና ደህንነት ምክሮች
የማርች 2020
ቁጥር 2፣ ጥራዝ 2
እራስዎን ከCOVID-19 ይጠብቁ: እጅዎን ይታጠቡ!
እጅ መታጠብ የጀርሞችን ስርጭት ለመከላከል ከሁሉም ስኬታማ መንገድ ነው። ንፁህ እጆች የጀርም መሰራጨትን ይከላከላሉ እና አካባቢዎን ይጠብቃሉ፡፡
- እጅዎን ቶሎ ይታጠቡ— በተለይ ጀርም ሊይዝዎት እና ሊያስፋፉ በሚችሉበት ጊዜ፡
- ምግብ ከማዘጋጀዎ በፊት፣ መሃል ላይ፣ እና በኋላ
- ምግብ ከመብላትዎ በፊት
- በቤት ውስጥ በተቅማጥ እና በትውከት የታመመ ሰው ከማስታመምዎ በፊት እና በኋላ
- ቁስል ወይም ቅድ ካማከምዎ በፊት እና በኋላ
- ቦታን ካፀዱ በፊት እና በኋላ – የፀዳ ቦታ ከመንካትዎ በፊት ፥ ያልጸዳ ቦታ ከነኩ በኋላ
- ሽንትቤቶችን ካፀዱ በኋላ
- ሽንትቤት ከተጠቀሙ በኋላ
- ዳይፐር ከቀየሩ ወይም ሽንትቤት የተጠቀሙ ልጆችን ካጽፀዱ በኋላ
- አፍንጫዎን ከተናፈጡ፣ ካሳሉ፣ ወይም ካስነጠሱ በኋላ
- እንስሳ፣ የእንስሳ ምግብ ወይም የእንስሳ ፅዳጅ ከነኩ በኋላ
- በኋላ የቤት እንስሳ ምግብ ከነካኩ በኋላ
- ቆሻሻን ከነኩ ወይም የቆሻሻ እቃን ከገለበጡ በኋላ
እጅዎን በትክክል ለመታጠብ አምስት ደረጃዎች፣ ሁልጊዜ፡
- እጅዎን በንፁህ ውሃ (ሙቅ ወይም ቀዝቃዛ) ያርጥቡ እናም ሳሙና ይቀቡ፡፡
- እጅዎን፤ የኋላ እጅዎን፣ የጣትዎችዎን መሃከል፣ እና የጥርፍርዎን ስር ጨምሮ በሳሙና ይሹ፡፡
- ቢያንስ እጅዎን ለ 20 ሴኮንዶች ይታጠቡ፡፡ የሰዓት ቆጣሪ ይፈልጋሉ? "መልካም ልደት"ን ሁለት ጊዜ ይዝፈኑ።
- እጅዎን በንጹህ፣ የሚፈስ ውሃ ስር ይታጠቡ፡፡
- ንፁህ ፎጣ በመጠቀም ወይም በአየር ማድረቂያ እጅዎን ያድርቁ፡፡
ሳሙና እና ውሃ መጠቀም ሳይችሉ ሲቀሩ ሳኒታይዘር ይጠቀሙ
ሳሙና እና ውሃ ካልተገኙ፣ አልኮልን መሰረት ያደረገ ቢያንስ 60 በመቶ አልኮል የሆነ ሳኒታይዘር ይጠቀሙ። በብዙ ሁኔታዎች ውስጥ ሳኒታይዘሮች በእጅ ላይ የሚገኙ የጀርሞችን ብዛት በፍጥነት መቀነስ ይችላሉ። ነገር ግን፣ ሳኒታይዘርዎች ሁሉንም የጀርም አይነቶችን አያስወግዱም፡፡ የእጅ ሳኒታይዘርን ለመጠቀም፡
- ፈሳሹን ወደ አንዱ የእጅ መዳፍ ያፍስሱ፡፡
- እጆችዎን በአንድላይ ይሹ።
- እጅዎ እስኪደርቅ ድረስ በሁሉም የእጆችዎ ቦታ ላይ ፈሳሹን ያዳርሱ። ይህ እስከ 20 ሴኮንዶች ይፈጃል።
Washington State Department of
Labor & Industries
ጥናቱን በተመለከተ ተጨማሪ ለማወቅ ወደ SHARP ይደውሉ/አጭር
የፅሑፍ መልእክት ይላኩ/ኢሜይል ያድርጉ
360-819-7908 • 1-888-667-4277 • JanitorStudy@Lni.wa.gov
SHARP ሪፖርት ቁጥር : 102-29-2020
SHARP
Safety & Health Assessment &
Research for Prevention